አህያ ፈሳች ብሎ ማን አፍንጫ ይይዛል?

አህያ ፈሳች ብሎ ማን አፍንጫ ይይዛል?
የጎንደር ህብረት የተባለው የሥራ ፈቶች ስብስብ የተመሰረተው የቅማንተን የማንነትና የራስ አስተዳደር ይገባኛል ጥያቄ በማስቆም ቅማንት ዛሬም እንደ ጥንቱ በማንነቱ እንደተሸማቀቀ ወይም በደባል የማንነት ድሪቶ ታፍኖ እንዲሞት ለማድረግ ነበር፡፡ መጀመሪያ ስለጎንደር ህብረት ሊታወቅ የሚገባው በሁለት ቢላዋ የሚበሉ የሶስት አለም ሰዎች ናቸዉ የጎንደር ህብረት ከፍተኛ የገንዘብ ደጋፊወች በኢትዮጵያ በግል የዉጭ ባለሀብትነት የተመዘገቡና በዉጭ የሚኖሩ በአማራ ክልል የተለያዩ ችሮታ የተረከቡ ከአንዳድ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋርም በጥቅምም ሆነ በዝምድና ግንኙነት ያላቸዉ ግለሰቦች ናቸዉ።  85 ፐርሰንቱ የመቶ አለቃ መላኩ ተፈራ የስጋ ዘመዶች ሲሆኑ 10 ፐርሰንቱ ደግሞ ከነዚህ የመላኩ ቤተሰቦች ጋር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በጋብቻ በአበልጅነት በማሀር ግንኙነት ያላቸዉ ከነሱ ለመራቅ በይሉንታ የተቀመጡ መሀል ሰፋሪ ናቸዉ። 5 ፐርሰንቶች ደግሞ በኢትዮጵያ እንድነት ስም ለግል የስልጣን ጥም የሚራወጡ ጭሆቶችን ሰምተዉ እዉነታዉን በማደን ላይ ያሉ ሁሉንም ጥያቄወች ለማወቅ የሚጠይቁ የሁሉም ብሄረሰብ ኣካላት ናቸዉ። ዝርዝራቸዉንና በዉጭ የሚያደርጉትን የሰሞኑን የዋሽንግተን ዲሲ የአራት ቀን ድስኩር ዘገባ እናቀርብላችሁአለን ድርጅቱ ውስጥ በመሪነት ደረጃ አብዛኛዎች ቅማንት እንዲሆኑና የቅማንትን ጥያቄ የሚቃወም ሌላ ቅማንት ያለ ለማስመሰል አሜሪካና ካናዳ አገር ያሉ ጽንፈኛ የቤተ አማራ፣ ቤተ አማራ መድን፣ ዳግማዊ መዓድ፣ ሞረሽ ወገኔ፣ ወዘተ የተባሉ ትምክህተኛ ድርጅቶች በጋራ ተነጋግረው የኮመሰሷት ተንኮል እንደሆነች ተደርሶባታል፡፡ እናም የጎንደር ህብረት የተባለው ድርጅት በእነዚህ የትምክህት ሃይሎች ተጠፍጥፎ የተሰራ ልሙጥ ቡድን ነው፡፡ እሾህን በሾህ በሚባለው አስተሳሰብ ተመስርተው ቅማንትን በራሱ ሰዎች ለማስወጋት ታቅዶ ሰው ሲፈለግ በየነ አስማረ እና አበበ ንጋቱ የሚባሉ ቅጥረኛ ባንዳዎች ዓይናቸውን በጨው አጥበው “እኛ አማራዎች ነን ባንሆን እንኳ መሆን እንፈልጋለን” በማለት የጎንደር ክስረትን የመሪነት ሃላፊነት ተረከቡ፡፡
ይህን ድርጅት በአባልነት ከሰበሰባቸው ሰዎች መካከል አብዛኞቹ የድሮው ጨለምተኛው ኢህአፓ አባላት የነበሩና አሁን በእርጅና ምክንያት ከቤታቸው የሚውሉ ነገርዓለሙን የሳቱ ጂጁዎች ይገኙበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በእነዚህ ጅጁዎች የቡና ወሬ የተሳቡ ጥቂት ወጣቶችና ሴቶች አሉበት፡፡ ሌላው ቡድን ደግሞ “የአማራ እንባ ጠባቂ ነን” የሚሉት የጽንፈኛው የቤተ አማራና ሌሎች ድርጅቶች አባላትም ይገኙበታል፡፡ በዋናነት ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆነው የሚሾፍሩት እንዚህ ጽንፈኞች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህን እንዳይታወቅባቸው ልዩ ልዩ ታክቲኮችን ይጫወታሉ፡፡ ለምሳሌ ቤት አማራ የሚባለው ድርጅት ከጎንደር ህብረት እንቅስቃሴ ውስጥ ምን አይነት ተሳትፎ እንደሌለው ለማስመሰል በየፌስ ቡካቸው የጎንደር ህብረትን ያጥላላሉ፡፡ ለምሳሌ “አመራሩ አማራን አይወክልም ቅማንት ነው” እያሉ ያራግባሉ፡፡ ነገር ግን ይሄ ተንኮላቸውን መሸፋፈኛ (cover-up) እንጂ ቤተአማራ ጎንደር ህብረትን ጠልቶት አይደለም፡፡ ዋናው ዓላማቸው “የቅማንትን ጥያቄ ቅማንቱ ራሱ እየተቃወመው ነው” ብለው ቅማንቱን ለማደናገርና ጥያቄውን ለማስቀልበስ ነበር፡፡
የጎንደር ህብረት ለባንዳዎቹ የሚሠጠው አገልግሎት አንድ እና አንድ ብቻ ነው፡- ዶላር መሠብሰቢያና ወደ ሃገር ውስጥ የላኩ በማስመሰል መቀምጨል ብቻ ነው፡፡ እነሱ ዶላር እያዋጡ ለሚያስረክቧቸው የዋሃን ዲያስፖራዎች ሥራ የሠሩ ለማስመሰል ሚዲያዎች ላይ ያራግባሉ፤ ሪፖርታቸውን ያሳምራሉ፤ ከዶላር ምንጮቻቸው ፊት የቅማንት ጉዳይ በቁጥትና በንዴት ያራግባሉ፤ ምንም ያልተሰሩ ወይም ሊሆኑ ከቶ የማይታሰቡ ነገሮችን እንደሚሆኑ አድርገው ሪፖረት ያደርጋሉ፡፡ ምስኪኑ ዲያስፖራ ሃገር ቤት ስላለው ሁኔታ ትክክለኛ መረጃ ስለሌለው ባንዳዎቹ የሚግቱትን ወሬ ብቻ እየተቀበለ ይሄዳል፡፡ ዶላሩንም እየመዘዘ ያስታቅፈዋል፡፡ አዎ አሁንም ጎንደር ህብት በዚህ ሂደት ውስጥ ነው መቀጠል የሚፈልገው፡፡
ይህ የጎንደር ህብረት የተባለው የጽንፈኛ ትምክህተኞች ከበሮ ቡድ በትክክል የቤተ አማራዎችና ሌሎች አካራሪ ድርጅቶች ሌላ ግልባጭ ለመሆኑ የምትረዱበት መንገድ ሁለቱም የሚያወሩትና የሚቦተልኩት ስንመለከተው አንድ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ ይሄውም “ወያኔ ቅማንትን ተጠቅሞ አማራን ሊያዳክም ነው፤ ወያኔ የሱዳንን ድንበር ለመቆጣጠር ነው፤ የጎሳ ፖለቲካ ነው፤ ወዘተ” እያሉ ማስተጋባት ነው፡፡ እነዚህ አባባሎች በሙሉ በሌሎች ትምህተኛ ድርጅቶች ሲባሉ የነበሩ አሁንም እየተብላሉ ያሉ ናቸው እንጂ የጎንደር ህብረት የተባለው የባንዳ ድርጅት የራሱ ማኒፌስቶ አዘጋጅቶ እየታገለ አይደለም፡፡ ሲጀመር ይህ የጎንደር ክስረት የተባለው የባንዳ ድሪቶ ለባሽ ድርጅት የተመሠረተው “የሰብአዊ እርዳታ ድርጅት” በሚል የአሜሪካን መንግስት አጭበርብሮ ነበር፡፡ ነገር ግን የሚሰበሰበውን ገንዘብ ከመቶው 60ውን ባንዳውና ጽንፈኛው እዛው ተከፋፍሎ ያዳፍነውና የቀረውን 40 በመቶውን አገር ውስጥ ለነበሩት ሽፍቶችና አስመሳይ አብዮተኞች ያከፋፍላል፡፡ እናም በዚህ ረገድ ስንገመግመው የጎንደር ክስረት የፖለቲካ ወይም ግብረ ሠናይ ድርጅት ሳይሆን ለትርፍ ያልተቋቋመ አትራፊ ድርጅት ነው፡፡ ይሄውም የዶላር ወተት ከየዲያስፖራው እያለቡ መጠጣት ነው፡፡ ልብ በሉ! ይህ ድርጅት በትክክል የሰብአዊ እርዳታ ለመስጠት የተመሠረተና ለጎንደር አንድት የሚታገል ቢሆን ኖሮ ባለፈው ችግር ላይ ለወደቀው የቅማንት ህዝብ ድጋፍ ያደርጉ ነበር፡፡ ነገር ግን ከአመሠራረታቸው ቅማንትን ለማጥፋት ስለነበር አንድም ነገር አላደረጉም፡፡ ይልቁንም ቅማንቱን ለማሥጨረስ እነ የሞት አለቃ ደጄኔን አደራጅተው በመላክ ቅማንቱ ላይ ተጨማሪ ጥፋት ለማድረስ ታተሩ፡፡ ነገር ግን የምስኪኑ ቅማንት አምላክ ቅርብ ስለሆነ ይህን ደጀኔ የተባለውን አረመኔ በበረሃ አስቀረው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቅማንት እንቅስቃሴ የሚደናቀፍበትን ማንኛውንም ሥራ እየሠሩ እስከአሁኗ ሠዓት ደርሰዋል፡፡ አሁን ምን እያደረጉ እንዳሉና ለወደፊቱ ያቀዱት ምን እንደሆነ ወደ ኋላ እመጣበታለሁ፡፡
እንግዲህ ከላይ እንደገለጽሁኩት የጎንደር ህብረት ውስጥ ያሉትን ሰዎች በሦስት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ አንደኛው ጽንፈኛው የትምክህት ሃይል ሲሆን የድርጅቱ ትክክለኛ ዓላማም የእነዚህ አካላት ብቻ ጉዳይ ነው፡፡ እነሱ የሚፈልጉት በቅማንት ስም ተመስርቶ ስለ ትምክህተኛው አስተሳሰብ የሚያራግብላቸውና የቅማንትን እንቅስቃሴ በቻሉት ነገር ሁሉ (by cook or by crook) ማደናቀፍና ቅማንትን ማጥፋት ብቻ ነው፡፡ እነዚህ አካላት አገር ውስጥ ካሏቸው ሆድ አደር አባሎቻቸው ጋር በቀጥታ በመገናኘት መመሪያ የሚሰጡ ናቸው፡፡
ሁለተኛው አካል ላይ ላዩን የድርጅቱ አመራር የሚመስለው (pseudo-leaders) እና የቅማንትነት ካባ የለበሰው የትምክህቱ ፈረስ (traitors) ሲሆን ጎንደር ህብረትን የተጠጋውም ዓላማው ገዶት ሳይሆን ሆዱን ለመሙላት (parasitic members) ብቻ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ህሊናቸውን ሽጠው ሆዳቸውን ስለሚሞሉ ቅማንት ወገኖቻቸውን በዶላር የሸጡ ናቸው፡፡ እነሱ የሚመሩት “የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው” በሚለው ብሂል መሠረት ስለሆነ ወላጆቻቸውን፣ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውን፣ ወገኖቻቸውን ለትምክህት ፍሪዳነት በዶላር የሸጡ ከሃዲያን ናቸው፡፡ መሠረታዊ ዓላማቸውም የመሪነቱን ቦታ በይስሙላ ይዘው የምትመጣውን ዶላር መቆርጨም ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱን የሚፈልጉትም ዶላር እስካገኙ ጊዜ ድርስ ነው፡፡
ሦስተኛው በእነዚህ ካሃዲያንና በጽንፈኞቹ ድርኩር ተታለው በተራ አባልነት ተጃምለው የገቡትና የከሃዲያኑና የጽንፈኞች የገቢ ምንጭ ሆነው የሚያገለግሉት ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ብዙዎቹ አሁን ያለውን ሥርዓት በጭፍን የሚጠሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ ቀደም ሲል ሃገሪቱን ለቀው የወጡና አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ሳይገነዘቡ ኢሳትና ሌሎች የሽብር ድርጅቶች የሚነዙትን ወሬ ብቻ በመያዝ ከድርጅቱ ጋር የተቀላቀሉ ናቸው፡፡ በዋነነት እያዋጡ የሚሠጡት ገንዘብ ምን ላይ እንደዋለ ወይም ለነማን እንደሚሠጥ ሁሉ ግንዛቤው የላቸውም፡፡ ብቻ እነሱ እንዲህ በማድረጋቸው ለሃገራቸው የበኩላቸውን እየተወጡ ይመስላቸዋል፡፡ “ለምላጭ የሰጡት ገላ” አይደል የሚባለው! እነዚህ አዝማሪው “ሳውቀው ገብቻለሁ እንደ ጥሬ በእጇ፤ ወይንም ታንፍሰን ወይ ታስጣኝ ከደጇ” እንዳለው እንደ ሆልስቴን ፍሬዣ ላም በየወሩ ደህና የዶላር ወተት ይታለባሉ፡፡ የሚገርመው ደግሞ አላቢው ሆዳም ባንዳ ስለሆነ ሙልጭ አድርጎ ነው የሚያልባቸው፡፡ ለጥጃቸው ይትረፍ አይልም፡፡ “ጥጃው በምን ይደግ?” የሚለው ለባንዳው ጣጣው አይደለምና፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ የጎንደር ክስረት የተባለው የጽንፈኛ ትምክህተኞች ፈረስ በጣም ተደናግጧል፡፡ ተብረጅርጇል፡፡ ሃይድሮፎቢያ እንደያዘው ውሻ አሁን የሚያደርገውን አያውቀሙም፡፡ ዝም ብሎ ያገኘውን ይሞነጫጭራል ፌስቡኩ ላይ ይለጥፋል፡፡ ተራ ግለሰቦችን ሁሉ ስም እያነሳ ይለጥፋል፤ ያስለጥፋል፡፡ ጎንደር ላይ እሳተ ገሞራ ላፈነዳ ነው ይላል፡፡ ወይ ማበድ ሰው ተፈጥሯዊ የሆነውን ነገር ሁሉ አዘዋለሁ ሲል ይገርማል፡፡ ከዚህ በፊት መከራውን አይቶ ታግሎ የቅማንትን ጥያቄ ማስቀልበሰ ያልቻለባቸውን ፕሮፓጋንዳዎች ዛሬ እንደገና መልሶ እንዳዲስ ማራገብ ጀምሯል፡፡ “የቅማንት ኮሚቴ መቀሌ ቢሮ አለው፤ ህወሃት በጀት መድቦለት ነው የሚሰራው፤ በየትልልቅ ከተሞች የቤት መስሪያ ቦታ ተሰቶታል፤ የደህንነት ስልጠናዎችን ወስደዋል፤ የጦር ልምምድ በጋባና ጨንጮቅ መካከል ባለው ቦታ እያደረጉ ነው፤ ወዘተ” እያሉ ያናፍሳሉ፡፡ አሁን ሁኔታው ባሰቡት መንገድ አልሄድ ስላላቸውና የቅማንቱ ጉዳይ ለህዝበ ውሳኔ መዘጋጀቱ አሳበዳቸው፡፡ ባንዳው ፈልጎ የነበረው የቅማንት ጉዳይ በተንጠልጠል አየር ላይ እንዲቆይለት ነበር፡፡ ባንዳው የቀመረው ቅማንቱ ጥያቄውን እንዲቀጥል፤ ክልሉ ደግሞ ሲያንዛዛው እንዲኖር በማድረግ ጉዳዩ አላለቀም እያሉ የዲያስፖራዋን የዶላር ወተት መጋት ነበር፡፡ ነገር ግን ባልጠበቁት ሁኔታ ቅማንቱ ተስፈንጥሮ አመለጣቸውና ዶሴው ሊዘጋባቸው ስለሆን ተርበተበቱ፡፡ ምናልባትም ሌላ የገቢ ምንጭ ሳያፈጥሩ የቅማንት ጉዳይ ካለቀ አበቃላቸው ማለት ነው፡፡ የወልቃይትን ጉዳይ አራግበው ከሰሩ፡፡ በዛ ሲናደዱ የቅማንቱ ጉዳይ ቶሎ ማለቁ አስደንግጧቸዋል፡፡
እንግዲህ እነዚህ ባንዳዎች እንደፖለቲካ የቅማንት ህዝብ መብቱን ማግኘቱ አለማግነቱ አያስጨንቃቸውም፡፡ ይህ የሚያስጨንቀው ለጽንፈኛው የዘውዳዊው ሥርዓት ናፋቂ ቡድን ብቻ ነው፡፡ ለባንዳ ግን የሚያስጨንቀው ሳይሰራ ቁጭ ብሎ እንደ ጡረተኛ ወሬ ብቻ አውርቶ የሚሰለቅጠው የዲያስፖራ ዶላር መምጣት አለምምጣት ብቻ ነው፡፡ በእርግጥም አበበ ንጋቱና በየነ አስማረ አሁን ሊደነግጡ ይገባቸዋል፡፡ እነሱ አእምሮ ሳይሆን ጨጓራ ብቻ ነውና ያላቸው፡፡ የጎንደር ህብረት የሚያራግበው ፕሮፓጋንዳ ካጣ የእነ ባንዳው አበበና በየነ የዶላር ምንጭ ይዘጋል፡፡ ይህ ደግሞ ለእነሱ ሞት ነው፡፡ እናም አሁን በቅማንት ጉዳይ ፈርስ ላይ ተሰባስበው እንደሚጓጉሩ ከብቶች እየተንጫጩ ነው፡፡ በእነሱ እሳቤ አሁን ሁለት ነገሮችን በአንድ ጊዜ ለማከናወን አቅደው እየሰሩ ይገናሉ፡፡ አንደኛው የቅማንትን ዴሞክራሲያዊ ትግል አስተባብረው እዚህ ያደረሱ የኮሚቴ አባላትን ሥምና ፎቶ በየፌስቡካቸው በመለጠፍ ማራገብ ሲሆን ዋና አላማውም ሕዝበ ውሳኔው በትክክል እንዳይካሄድ ማደናቀፍና እንደተባለው የቅማንትን ጉዳይ የእድሜ ልካቸው አጀንዳ በማድረግ የጡረታ ምንጫቸውን ዘላቂነት ማስጠበቅ ነው፡፡ ባንዳ ሲያስብ ቢውን ከሆዱ አያልፍም አይደል! በቃ እንዲህ ናቸው፡፡
ሁለተኛው የቅማንት ምሁራንን በተለይም ጎንድር ዩኒበርሲቲ ውስጥ ያሉትን ስምን ፎቶ በየፌስቡኩ ላይ በመለጠፍና ከህወሃት ጋር ወግነው አማራን እያስጨፈጨፉ ነው የሚል ቱሪናፋ በመልቀቅ ድርጅቶችን የብጥብጥ ማእከል በማድረግ በመካከል እድሉን ተጠቅመው የቅማንትን ጥያቄ ማጨናገፍ፤ ማለትም ማራዘም መቻል ነው፡፡ ለባንዳው ሁለቱም ውጤታቸው አንድ ነው፡፡ ከተሳካላቸው የቅማንትን ጥያቄ አየር ላይ በማቆየት ቋሚ የዶላር ምንጭ ማድረግ ብቻ ነው፡፡
በአጠቃላይ ለጎንደር ክስረትና ለጽንፈኛው የትምክህት ቡድን በያሉበት የምመክራቸው በከንቱ ፈሳቸውን እንዳይጨርሱ ነው፡፡ የቅማንት ጉዳይ አለቀ ደቀቀ፡፡ ከእግዲ ወዲህ ቅማንትን የዶላር ምንጭ አታደርጉትም፡፡ ሌላ አጀንዳ ፈልጉ፡፡ ምናልባትም የአገው ስርዎ መንግስት ተመልሶ ሊመጣነው፤ ወይም ነገደ ወይጦው መብቴ ይከበርልኝ የሚል ጥያቄ ሊጠይቅ ነው፤ ወይም ጋፋቴው ማንነቴ ይከበር ሊል ነው፤ ወይም ሌላ የሚሻላችሁን ፈልጉ፡፡ ለዶላር መሰብሰቢየ የሚመቻችሁን እናንተ ታውቃላችሁ፡፡ በቅማንት ስም መነገድ ግን በቃ ። በመጨረሻም የቅማንት ህዝብ እዚህ የደረሰዉ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እኩልነትን አምኖ ከእህት ወንድሙ የአማራ ህዝብ ጋርም ችግሮችን በመማከር በመግባባት ይሁሉንም መብት በማይጋፋ ምልኩ ልጆቹንና ህዝቡን ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን ከመቸኮል ትእግስትን ለመጥፎ ተናጋሪወች መቻቻልን እያስተማረ ብዚህ አስተምሮቱ እየሞተ እየታሰረ በአሁኑ ሰአት የቅማንት የማንነት ጥያቄ ከብሄረስአቡ ወጥቶ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ጥያቄ ሆኖአል። አንዳንድ የኮሚቴ አባላትን ወይም ታዋቂ የቅማንት ሰዎችን እንገድላለን እያላችሁም ስታንቧትሩ እየሰማናችሁ ነው፡፡ ሲጀመር የቅማንት ህዝብ ሁሉም ኮሚቴ ነው ያጨበጨበላችሁ ሁሉ ነገ ቁሞ ይመሰክርባችሁአ፡፡ ይህን አላረፋችሁትም፡፡ በሉ አትጃጃሉ፡፡ “ቅማንትን ለማግኘት 76ን ይጫኑ፡ ይቅርታ! ቅማንቶች በአገራቸዉ ጉዳይ ቢዚ ናቸዉ! እባከዎ ጥቂት ቆይተው ይሞክሩ ከባንዳ ይልቅ ባንዳውን የገዛው ዶላር ይሻላል!

ፍሊፕ ሶቅራጦስ

Top of Form

 

Bottom of Form

 

Leave a Reply