እራስን ሳይለዉጡ ለዉጥ ፍለጋ የዲያስፖራው ዉሎ

ከእንቆጳ ቴዎድሮስ

03/16/2017

” የተፃፉት ሁሉ እዉነተኛ አይደሉም። እዉነታውን ሳናስተምር የተፃፉ ታሪኮችን ብቻ ብናነብ ትዉልድን ከመግደል ሌላ ለልጆቻችን እራሳችን ደብቀናል ለትዉልዳችን እዉነትን አንደብቅ፤”
ይህን ለማለት ያስገደደኝ እዉነታ ነዉ፤ ከሁለት ታዋቂና ተፅኖ ፈጣሪ የአለም መሪዎች ንግግር ልነሳ፤ የጥቁሮች የነፃነት ታጋይ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ከመሞታቸዉ በፊት የመጨረሻ ንግግራቸዉ አሁን ከማቀርብላችሁ እዉነታ ጋር ሲገጣጠም እንዲህ የሚል ነበር። “ I have been to the mountain Top” ከትግሉ የመጨረሻ ጫፍ ደርሸ ነበር፤ ከባድ ፈተናዎች ፊታችን ላይ ይጠብቁናል፤ ትግላችን በሰላማዊ መንገድ መቸዉንም በማንም አይቆምም። እንደማንኛዉም ሰዉ ብዙ አመታትን መኖር እሻለሁ። ይህ አሁን እኔን አያስጨንቀኝም መብታችን በቅርቡ እናስጠብቃለን እንዳሉ ሲያልፉ፤ ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ለተከታያቸዉ ትራፕ በአጭር ሀረግ ስለ ሰዎች መብት እንዲህ ነበር ያስጠነቀቁአቸዉ፤ እኛ የታገልነዉ አሉ “የተለየ ጥቅም ለማግኘት ሳይሆን እኩል መብት እንዲኖረን ነዉ፤ we don’t ask special treatment we struggle for equality.” የነዚህ የአለም ተጽኖ ፈጣሪ መሪዎችን ንግግር በመግቢያነት የተጠቀምኩት እዉነትን እያወቁ ታሪክና ህዝብን የሚቀብሩ ከእዉነት እርቀዉ ለራሳቸዉ ሳይሆኑ ምቀኝነት የተጠናዎታቸዉ ከሀገር እርቀዉ በተደላደለ አለም የሚኖሩ የቤተ አማራ የሰሞኑ ንትርክ ሰማሁና እንዴ እዉነተኛ አማራዎችም አሉ? ለቅማንት ብሄረሰብ የማንነት ጥያቄ ያገባናል የሚሉ? እራሴን ጠየኩና ክርክራቸዉን ማዳመጥ ቀጠልኩ።
ወይዘሮዋ ንግግራቸው የሚያስለቅስ ልብ የሚነካ ነበር። የቅማንት ብሄረሰብ የማንነት ጥያቄ ከእሩብ ምእተ አመታት በላይ መጨረስ አልነበረበትም መብታቸዉ እንዳይጠበቅ እኛም የሰራነው ትክክል አልነበረም ቅማንት ቅማንት እንጂ አማራ አይደለም አልነበረምም። በርግጥም ተጋብተናል፤ ተዋልደናል። ከነጭ ከአረብ፤ ከቻይና አልተዋለድንም እንዴ? በቅማንት የማንነት ጥያቄ እኛን የሚያንገበግበን ምንድነዉ? በተለይ ደግሞ እኛ አማራ ነን እያልን አሁን የምናነሳዉ የአማራ የማንነት ጥያቄ ቅማንቶች ከሚሞቱበት ከሚታሰሩበት የተደበቀ እዉነታ አለን እንዴ? ይልቁንስ ከጎናቸዉ ሆነን መታገል ነበረብን። ስህተቴ ከሆነ እኛም አሁን አማራ ነኝ ብለን የምናወራው ለይስሙላ ይሆናል። ለገንዘብ መለመኛ ማንነቴን እየተጠቀሙብኝ እንቅልፍ ነስቶኛል፤ቅማንቶች የጠየቁት የመብት ጥያቄ ነዉ ስንል የወያኔን ደጋፊ ስንባል፤ ቅማንትና አማራ መለያየት የለባቸዉም ሲባል ግንቦት 7 ፀረ ሰላም ስንባል አሁን ለይቶልን ከቅማንቶች የሩብ አመት ጥያቄ ተቀላቀልን። ፖለቲከኞችም ብትሆኑ ስለህዝብ ጥያቄ ኣቑም እና ግልጽ መልስ ሳይኖራችሁ ህዝቡን አታስጨርሱ፤ አማራ አማራ እንጂ ትግሬ፤ ቅማንት፤ ኦሮሞ አይደለም አልን። እሽ ተስማማሁ አማራ ነኝ። ከራሳችን ጋር እንታረቅ አማራነታችን መለመኛ መሆኑ እዚህ ላይ መቆም አለበት የሌሎችን መብትም በመጠበቅ ከራሳችን ጋር እንታረቅ የሚያሰጋኝ የቅማንት መብት በከበር ሳይሆን የጎንደር አማራ የሽዋ አማራ የጎጃም አማራ በመባባል እየተበጣጠስን መነሻና መድረሻችን ገንዘብ ብቻ ሆኖ የኛ መጨራረስ ነዉ የሚያስጨንቀኝ በማለት ነበር

ንግግራቸዉን የቆጩት።
ዶ/ር ማርቲን ሉተር አዲሲቱን ኢትዮጵያ በአሜሪካኖች ስም እንዲህ ነበር ያዩት ከእለተ ሞታቸዉ በፊት፤ ለአሜሪካዊያን የምናስተላልፈዉ መልእክት በአጭሩ “እዉነቱን ተናገሩ” እኛ ጥቁሮች የምንኖረዉ ቻይና? ራሻ? ወይስ ቶታሊተሪያን ሀገሮች ነዉ? ሲሉ ጠየቁ። የቅማንት የማንነት ጥያቄምንም በተመሳሳይ መንገድ ለማደናቀፍና ለማፈን በሌሎች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እንዲጠላ በሬ ወለደ ፕሮፓጋንዳዎች ተሰርተውበት የማንነቱ ጥያቄ እሩብ አመታትን አስቆጥሩል። ለግንዛቤ ያህልም ቅማንት ሀገሩ ግጽብ ነው፤ ቅማንት ጂራት አለዉ፡ ቅማንት እንጨት (ወይራ) እንጂ ሰዉ አይደለም፤ ቅማንት ትግሬ ያስቀመጠዉ ከአማራ የተገነጠለ ቡድን እንጂ ብሄር አይደለም፤ቅማንት በአማራ ተዉጦ ዘሩ ጠፍቱዋል፤ ቅማንቶች ይህን ጥያቄ አሁን ያቀረቡት ወደ ትግራይ ለመገንጠል ነዉ በማለት ቅማንት በሌሎች እንዲጠላና እንዲጠረጠር ከአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት እስክ ዲያስፖራ የኢሳት፤ ጎንደር ህብረት(የጎንደር ጥፋት ) ወይም ጎንደር ዉድመት ግንቦት ሰባቶች ያልቆፈሩት አልነበረም። መሬት ስትቆፍር አታጥልቀዉ መጀመሪያ የሚገባበት አይታወቅምና ይሉሀል ይህ ነዉ።
ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ለቅማንት ብሄረሰብ ማዉራት አሳዉን ላጥማጁ ይተዉት ማለቱ
ይቀላል። ታሪኩ ሙሉ በሙሉ በትክክል በታሪክ አለመፃፉ ቢያሳዝንም በመግቢያነት የተጠቀምኩት ጥቅስ እንዲያስቡ፤ እንዲመራመሩ እና እዉነታዉን ለልጂዎ እዲያስተምሩ የገሀዱ አለም ያስገድደዎታል። ቅማንቶች በኢትዮጵያ አንድነትና ክብር ጉዳይ ከአብራኩ ከወጣዉ አፄ ቴውድሮስ ጀምሮ እንደምንረዳው አንደራደርም። አፄ ቴዎድሮስ ቅማንት ነው እንዴ? እራስዎን ሊጠይቁ ይችላሉ። የመሳፍንት ታሪክ ፃህፍታን የጌቶቻቸዉን ትእዛዝ ይፅፉ ነበርና እዉነት ቦታዋን አጥታ ተንሳፋ እናያታለን። ስለ አፄ ቴዎድሮስ ነገስታቶች በትእዛዝ ካፃፉት የንቀት ጥቅስ አንድ ልበላችሁና ምርምሩን ለናተ ልተዉላችሁ አንባቢዎቸ። “ ሺ ጦር ከሁላዉ ሽ ጦር ከፊቱ ይህን ሳታይ ሞተች ኮሶ ሻጭ እናቱ፤” ትላንት የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችን እንዲህ ዝቅ አድርገዉ ያዩ ከነበሩ ጋር ነዉ አሁን ድረስ የቅማንት ብሄረሰብ ከአማራ ክልል መንግስት የተወሰኑ ባለስልጣናት የጎንደር ህብረት ለጥፋት ባለጉርሻ ተደራሾች (የዶላር) ጋር ግብ ግብ ገጥሞ ከሞላ ጎደል ህገ መንግስታዊ መብቱን የህገመንግስቱን የበላይነት ለማስመለስ በሰላማዊ መንገድ እየሞተም፡ እየታሰረም፡ እየተፈናቀለም እየታገለ ያለዉ፡፡ በመከባብር በመተሳሰብ አብሮ ለመኖር እንደዚህች እህታችን እዉነተኛ የአማራ ልጆች በተለይ ወጣቶች በቅማንት የማንነት ጥያቄ ላይ ከጎናችን መሰለፍ አለባችሁ። ዝምታውን ሰብራችሁ የሚያራርቁን ይህን እናዳደርጋለን በማለት ከኪስዎ በወሰዱት ገንዘብ ከእህት ወንድሞቻችሁ የቅማንት፤ የትግሬ፤ የኦሮሞ ብሄርሰቦች ጋር የሚያራርቁህን ስለ ዲሞክራሲ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ ድርሻችሁን መወጣት ይጠበቅባችሁል። እኛም እንደምናምነዉ አማራ ለሌላዉ ብሄረሰብ ታማኝ የሚሆነዉ ከአብራክህ(ሺ) ለመብቱ እየሞተ እየታሰረ ያለዉን የቅማንት የማንነት ጥያቄ ስትደግፉ ብቻ ነዉ። የቅማንት የማንነት ጥያቄ እንዲታፈን የክልሉን መሪዎች ለአድልዎና ለኢፍትሀዊ አሰራር እንቅፋቶችን አብረን በመታገል መንግስትንና ኢፍትሃአዊ አሰራሮችን ህዝቡ ማስቀየር እንዲሻሻሉ ማድረግ ይችላል። ህዝብን፡ ወይም አንድን ህዝብ ጠልቶና አፍኖ ለስልጣን የሚሮጥ ፖለቲከኛ ብቻዉን እንደሚሮጥና የሚቀድመዉም እንደሌለ መገንዘብ ግድ ይላል። በሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች የተመሰረተች ሀገራችን ከጥፋት ማዳን ይጠበቅብናል። አዎ አማራ አማራ እንጂ ሌላ አይደለም። ቅማንት አገዉ እንጂ አማራ አለመሆኑንም መቀበል ግድ ይለናል። ኢትዮጵያዊነታችን ደግሞ ደማችን መሆኑን ማሳወቅ ግዴታአለብን።

መልካም ንባብ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

Leave a Reply