በሁለት ቢለዋ የሚበሉት የሁለት ዓለም ፖለቲከኞች

ጎንደር ህብረት በገንዘብ ኢሳት በፕሮፓጋንዳዉ ብአዴን በጉልበቱ የሶስት ዓለም ፖለቲከኞች በቅማንት ብሄር ላይ የከፈቱት ዘመቻና ሰቆቃ ከብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጋር ህጋዊ ፍች እስካልፈጸመ ድረስ ለዘመናት ይቀጥላል!
ሃገራችን በዘረጋችዉ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርአት አብዛኞቹ ብህር ቤህረሰቦች ማንነታቸዉ ተረጋግጦ እራሳቸዉን በራሳቸዉ ማስተዳደር ከጀመሩና በፌዴራላዊ ስርአቱ ተጠቃሚ ከሆኑ ድፍን 26 አመታት ተቆጠሩ፡፡የቅማንት ህዝብ ከማለዳዉ ጀምሮ በተዘረጋዉ ዴሞክራሲ ስርአት እና ብህር ቤህረሰቦች ባጸደቁት ህገ-መንግሰት መሰረት በፍጹም ሰላማዊነት ህግን በማክበር ማንነቴ ይከበር እራሴን በራሴ ላስተዳድር ይገባል በማለት እየታገለ ቢሆንም ህገ-መንግስታዊ ጥያቄዉ ግን እንዲህ በቀላሉ እዉን ሊሆን አልቻለም፡፡ምክኒያቱ ደግሞ “ቅማንት ቅማንትነቱ ከተረጋገጠና እራሱን በራሱ ካስተዳደረ አማራ ይጠፋል” የሚለዉ መሰረተ ቢስ የትምክተኞች ፐሮፖጋንዳ ቅማንትን ለዝር ማጥፋት እልቂትና ተዘርዝሮና ተቆጥሮ ለማያልቅ ኢ-ሰባዊ ግፍ አጋልጦታል፡፡
ቅማንት እንደ እድል ሆኖ የመሬት ተስፋፊዎች የመሸጉበትና ሌላ ሃገር ለመመስረትና ህገ-መንግስቱን ለመናድ ክልሉን ከሚመራዉ ድርጅት ጋር በመቀናጀት ቅማንትን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ቃልኪዳን ያሰሩበት ዞን በመሆኑ ትግሉን ዉስብስብና እስከ ሂዎት መሰዋትነት እንድንከፍል ተገደናል፡፡በቅማንት ህዝብ ላይ ጨዋዉ የአማራ ህዝብ ያልወከላቸዉ ጥቅመኞችና ስልጣን ፈላጊዎች በሙሉ ማላትም ጎህ፣ቤተአማራ፣ሞረሽ ወገኔ፣ሰማያዊፓረቲ፣መአድ፣አርበኖች ግንቦት 7…ወዘተ ተዘርዝሮ አያልቅም የተባሉ ጽንፈኛ ድርጅቶች ከብአዴን ጋር መስመራዊ ቅንጅት በመፍጠር ኢሳት፣ቨኦኤ፣የጀርመን፣ድምጽ፣የአማራ ማስ ሚዲያ፣የተለያዮ ኦንላየን ቻናሎች፣ዋቭ ሳይቶችና ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም 24 ሰአት በቅማንት ህዝብ ላይ የጥላቻ ፖለቲካ ይሰብካሉ፣ህዝባችንን በጅምላ ያዋርዳሉ፣ይገድላሉ፣ይዘርፋሉ፣ህጻናትን በጠራራ ጸሃይ ይደፍራሉ በጥቅሉ አለም አክ ብሎ የተፋዉን ዘርን መሰረት ያደረገ ጥላቻ ይነዛሉ፡፡
ታጋሹ የቅማንት ህዝብ ግን ከዚህ መራራ ትግል በኋላ የሚገኘዉን ጣፋጭ ድል ፍሬ በማሰብ ብቻ ሲገድሉት ይሞታል፣ሲዘርፉት ይዉሰዱት ብሎ ዝም ይላል፣ሲያዋክቡት አንገቱን ይደፋል፡፡ብአዴንም ቅማንትንትን ጨምሮ ክልሉን እመራለሁ የሚል ድርጅት ሆኖ ሳለ በዴሞክራሲያዊ ካባ ተጀቡኖ ቅማንትም በብሄራዊ ጨቆና ዉስጥ እስካሁኗ ደቂቃ የወደቀ ቤህር ሆኖ እያለ እንደብህራዊ ጠላት በመቁጠር በግልጽ ጦርነት አዉጆበታል፡፡ብአዴን እሱ በሚቆጣጠረዉ ማስ ሚዲያና ጽንፈኞች አስተምሯቸዉን በሚያራግቡበት ሚዲያዎች የዴሞክራሲያዊነት ካባ ተላብሶ እታች ህዝባችን ላይ ግን ነብሰ ገዳይ ወንበዴዎችንና ጉጅሎችን ከምእራባዉያን ሃገሮች ካሉ ጽንፈኞች በሚዋጣ ዶላር መሳሪያ እየገዛ ያስታጥቃል በጠራራ ጸሃይ የቅማንትን ልጆች ያስገድላል፡፡ለዚህም ጭልጋ ወረዳ ገለድባ ከተማ ከህዝብ ዉሳኔዉ ማግስት ያስገደላቸዉ ወንድማማቾች ግልጸ ማሳያ ነዉ፡፡
ብአዴንና ጽንፈኞች ከ 1270 ዓ.ም የትምክህት ስርአት በይኩኑብአምላክ ከተመሰረተ ጀምሮ ሁሉንም ማንነቶችና እምነቶች አንድ የማድረግ የሚጠቀምበትን የሰዉ ልጆችን በጅምላ የማንቋሸሽ፣የማግለልና ስብእናን የማዋረድ ተግባር በዚህ በ21ኛዉ ስልጡን ዘመን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡በብዝሃነት ላይ የተመሰረተ አንድነት ለሃገራችን ልማት ወሳኝ ነዉ፤ለዚሁም የሃገራችን ቤህር ቤህረሰቦች ብአዴንን ጨምሮ የቃልኪዳናቸዉ ማሰራያ ቀለበት የሆነዉን የኢፊድሪ ህገ መንግስት አጽድቀዋል፡፡ ይሁን እንጅ ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ብአዴን/ቤትአማራ እንደሌሎቹ ቤህራዊ ድርጅቶች ይህን ብዝሃነትን ሚያስተናግድ ህገ-መንግስት ከልቡ አልተቀበለዉም፡፡ለዚህ ማሳያወቹ በቅማንትና በትግራይ ቤህር ላይ የፈጸመዉን ግድያ ግፍና በደደል ጎንድር ቀበሌ 18 ላይ ትግሬ በመሆኑ ብቻ የገዛ ቤቱ ተዘግቶበት ቤንዚን ተርከፍክፎበት በሳት የጋየዉ ወገናችን ፣አራስን እናት፣አዛዉንቶችን ፣እረኞችን እራሳቸዉን መከላከል የማይችሉ ቅማንቶችን በሳንጃ ሆዳጨዉን እያረደ የገደላቸዉ ፣እንስሳቶች የቅማንት ንብረት በመሆናቸዉ ብቻ በጥይት አረር እንደባለቤቶቻቸዉ እየተደበደቡ የተገደሉት ብአዴን ኢትዩጵያዊዉ ISIS ስለመሆኑ ከበቂ በላይ ማስረጃ ነዉ፡፡
ብአዴን በግልጽ ህገ-መንግስቱንና ብዙሃንነትን እንደሚቃወም ማረጋገጫዉ በህዳር 29 ቀን 2007ዓ.ም የብሄርና ቤሄረሰቦች ቀን በሚከበርበት እለት ለብሄር ብሄረሰቦች ያለዉን ንቀትና ጥላጫ ለማሳየት ከመላዉ የክልል 3 ዞኖች የተዉጣጣ አሸባሪ ሃይል በማሰባሰብና ገዱ የሚያዘዉን ልዩ ነብሰ በላ ጦር የቅማንትን አርሶ አደር ባህል ልብስ በማልበስና በማመሳሰል የሚኒሊክን ልሙጥና ብጫቂ ጨርቅ በማዉለብለብ ከጸንፈኛ ዲያስፖራ በተዉጣጣ ዶላር፣የመንግሰት ተሸከርካሪዎችን ጨምሮ ለትራነስፖር በመጠቀም ከ15ሽህ በላይ የጥፋት ሰራዊት በማዝመት የቅማንትን ህዝብ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዚ ለመደምስ “የዘመቻ ቅማንትን መደምሰስና ወደግብጥ ማባረር” ዘመቻ በመተግበር በህገ መንግስቱና በብሄር ቤህረሰቦች ላይ ያለዉን ንቀትና ትምክተኝነት የሚያሳይ ቁልጭ ያለ ምስክር የማያሻዉ ማረጋገጫ ነዉ፡፡
ይህ ብቻ ሳያንሰዉ እንደ ጎንደርና ባህር ዳር ባሉ ከተሞች ዉስጥ ለዉስጥ ቦዘኔዎችን፣ የባንክ ከፍተኛ እዳ ያለባቸዉን እንዲሁም የከሰሩ ነጋዴዎችን በህቡዕ በማደራጀትና ነዉጥ እንዲነሳ በማድረግ በግልጽ የሃገሪቱን ህገ-መንግስት እንደማያከብሩ የኢፌድሪን ሰንደቅ አላማ በማዉረድና በማቃጠል በየመስሪያቤቶቹና ለነዉጠኞቹም ነዉጠኛ መፎክር አዘጋጅቶ በማደል ሃላፊነት የጎደለዉ ተግባርን ሲፈጸም ሃይ ያለዉ አልነበረም፡፡ ይህ ቡድን አሁን በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ ባሰራጨዉ ካርታ ደግሞ ወደፊት ይህን ስርአት በማፍረስ ሊመሰርት ያሰበዉ ሃገር ከተከዜ መለስ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እንዲሁም ከፊል ጋንቤላን ያጠቃለለ ሲሆን በደቡብ ደግሞ አዲስ አበባን ተሸግሮ እስከ አዳማ ድረስ እንደ ሚለጠጥ ግልጽ አድረጓል፡፡ለዚህ እኩይ አላማ ተግባራዊነትም መላዉን ሰሜን ጎንደርን እንደ ላቦራቶሪ በመጠቀም አዋጭነቱንም በጨዋዉ የቅማንት ህዝብ ላይ ኢ-ሰባዊ ድርጊቶችን ግድያዎችን ወዘተ በመሞከር/excersices በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ዉድ የኢትዮጵያ ቤህር ቤህረሰቦችም ቅማንት እየተጋፈጠ ያለዉ የቅማንትን ታሪካዊ ጠላት ብቻ አይደለም፤የሃገራችንን ህዝቦች ጥንተ ታሪካዊ ጠላት ትምክህትን እንጅ፡፡በመሆኑም እየተፈጸመብን ያለዉን ግፍና በደል ሳትረዱት ትቀራላችሁ የሚል እምነት የለኝም፡፡ይህን ጽንፈኛ ሃይል እንደ ሙጀሌ ተባብረን ከነሸንኮፉ መንግልን እስካልጣልነዉ ድረስ የነገ ህልሙ እኛን ብቻ ማጥፋት ሳይሁን እናንተንም ያጠቃለለ ነዉ፡፡የዚህ ህለምኛ ቡድን ስርአቱን በማፍረስ የቀደመዉን የርስት ጉልት ስርአት መትከል እንደሆነ አላማዉ በግልጥ እየነገርን ስለሆነ ሃቁን ታጡታላችሁ የሚል ግምመት ለኝም፡፡
ባጠቃላይ የቅማንትን መብት የማፈንና ዘራችንና ማንነታችን መሰረት በማድረግ የማጽዳቱ ዘመቻ በብአዴን ከፍተኛ ጽንፈኛ ባለስልጣናት የሚመራ የረቀቀ ሴራ መሆኑ ግልጽ ነዉ፡፡ለዚህ ማሳያዉ ወያኔን እንጠላለን የሚሉ ጽንፈኛ ሃይሎች በትግራይና በቅማንት ህዝብ ላይ የዘር እልቂት እንዲከናወን መመሪያ የሰጠዉንና ያስጨፈጨፈዉን የክልላችን ፕረዚዳንት ተብየ እንደ ቤህራዊ ጀግና በመቁጠር ከብአዴን ጎን መቆማቸዉና ገዱን የአትንኩብን የአይናችን ብሌን ነዉ ዘመቻ ትልቅ ማረጋገጫ ነዉ፡፡እነዚህ ቡድኖች እነሱ ወያኔ የሚሉትን ከጠሉ እንዴት ነዉ ብአዴንንና ገዱን ወይም በብኣዴን ዉስጥ የተወሸቁ ትምክተኞችን/ጽንፈኞችን አትንኩብን የሚሉት፡፡እኔ እንደሚገባኝ ህወሃትና ብአዴን ወይም ሌሎቹ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ህገ-መንግስቱን በጋራ ያጸደቁና ለአንድ አላማ የተሰለፉ ናቸዉ ብየ ነዉ የማምነዉ፡፡
የቅማንትን የራስ አስተዳድር ለመመስረት በ 12 ቀበሌወች ዉስጥ የህዝበ ዉሳኔ እንዲካሄድ በጥምር ኮሚቴዉ ስምምነት መደረሱ የሚታወስ ሲሆን ብአዴን ከተላላኪዎቹ ጋር በመቧደን ከጋራ ስምምነቱ ዉጭ በ 8 ቀበሌዎች ብቻ እንዲከናወን አድርጓል፡፡የዚህ ህ/ዉሳኔ አላማም ማንነትን የሚወስን ሳይሆን የአስተዳደራዊ አማራጭን መወሰን ነበር፡፡ያ ማለት ደግሞ አንድ ቅማንት ወይም የአማራ ተወላጅ የሆነ ግለሰብ ማንነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ለአስተዳደራዊ ጉዳዮች ይመቸኛል ወደሚለዉ አስተዳደር በፍላጎቱ እንዲካለል ማድረግ ነበር፡፡ይሁን እንጅ ብአዴን ከፍተኛ በጀትና ካድሬዎቹን፣ፖሊሶችን፣ልዩ ልዩ ታጣቂዎቹንና ጨፍጫፊዉን በገዱ ብቻ የሚታዘዘዉን ልዩ ሃይል ወዳካባቢዉ በማዘመት ከመዝገባ ጀምሮ ልዩ ልዩ ኢ-ዴሞክራሲያዊ በደሎችን በመላዉ የቅማንት ህዝብ ላይ እየፈጸመ ይገኛል፡፡
ለአብነትም የቅማንት ህዝብ ሆ ብሎ ወጥቶ ለህዝበ ዉሳኔዉ እንዳይመዘገብ ቤት ለቤት በመዘዋወርና በየጎጡ ታጣቂ በማስፈር ወደምዝገባ እንዳይሄድና እንዳይመዘገብ ህዉከት መፍጠር፣የቅማንት ታዛቢወችንና የኮሚቴ አባላት በዛቻና በታጣቂ ሃይል ወደምርጫ ጣቢያዉ እንዳይጠጉ ማድረግና ቤት ለቤት በመዘዋወር ቅስቀሳ እንዳያከናዉኑ እስከ ማሰር የደረሰ በደል መፈጸም፣የምርጫ ጣቢያወችን ማእከላዊ ከሆነዉ ቦታ ብአዴን በስልጣኑ በማዛወር ህዝብ ወደማይደርስበት ቦታ በመቀየር ለህ/ዉሳኔዉ ተደራሽ እንዳይሆኑ ማድረግ፣ወደቦታዉ የተላኩ የምርጫ ቦርድ አባላትን ስራቸዉን በነጻነት እንዳያከነዉኑ በመሳሪያ አጅብ ዉስጥ በማድረግ ማሸማቅ፣ በተለይም ቋራ፣መተማና ጎንድር ከተማ ምርጫ ጣቢያዎች ነዋሪ ላልሆኑ የአማራ ተወላጆች ህጋዊ ያልሆነ መታወቂያ በማደል እንዲመዘገቡ በማድረግ በህ/ዉሳኔዉ ብልጫ ለማግኘት ተግተዉ ሌት ተቀን ስርተዋል፡፡በምርጫዉ ቀን ደግሞ ኮሚቴዎችን አስረዉ አንገላተዋል፣ህዝቡ ወደምርጫ ጣቢያ እንዳሄድ ነብሰ ገዳይ ታጣቂዎችን ቤት ለቤትና በየጎጡ በማዝመት የቅማንትን ተወላጆች የምርጫ ካርዳቸዉን እየነጠቁ በመቅደድ ከምርጫዉ ዉጭ አድርገዋቸዋል፡፡
በጣም የሚያስተዛዝበዉ ጉዳይ ምርጫ ቦርድ ወኪሎቹ ቀን ተቀን በቅማንት ህዝብ ላይ የሚደርሰዉን በደልና ማዋከብ በአካል በቦታዉ ተገኝተዉ እየተመለከቱና እያዩ እንዲሁም ከ11% በላይ ህዝብ ከላይ በተገለጹት ተጸኖዎች አማካኝነት ያልመረጠ መሆኑ የተረጋገጠ ሆኖ እያለ 4 ቀበሌዎች ከ 90 ፐርሰንት በላይ የቅማንት ህዝብ ሚኖርባቸዉ ብአዴን ምርጫ እንዳይከናወንባቸዉ ከዚህ በፊት ከተደረሰዉ የጥምር ኮሚቴዉ ስምምነት ዉጭ ስልጣንን ከህግ በላይ በመጠቀም የህዝብ ዉይይት ያስፈልጋል በማለት በሃይል ምርጫ ያልተከናወንባቸዉ መሆኑ እየታወቀ የምርጫ ቦርድ ምዝገባዉና ህ/ዉሳኔዉ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ነበር በማለት ኢ-ሚዛናዊ የሆነ መግለጫ ሰጥቷል፡፡በመሆኑም በእኔ እምነት ህ/ዉሳኔዉ ግቡን የመታ፣አሳታፊና ዴሞክራሲያዊ ያልነበረ፤ለትምክተኛዉና ለጸንፈኛዉ ቡድን የልብ ልብ የሰጠ ወደፊትም እመሰርተዋለሁ ለሚለዉ የቅጀት ሃገር እንደመንደርደሪያ ለሚያደርገዉ ሙከራ እንደ አድቫንቴጅ እንዲወሰድ ሆኖ አልፏል፡፡ ይሁን እንጅ ይህ ጉዳይ ለአካባቢዉ ዘላቂ ሰላም ይሰጣል ተብሎ አይታሰብብም፡፡እነሱ እንደሚሉት ምርጫ ቦርድ ዉጤቱን ሳይገልጥና ገና የህ/ዉሳኔዉ ሂደት ሳይቋጭ 7ቀበሌዎችን በነባሩ እንቆይ በማለት ህዝቡ ወሰነ ሚል ዜና በተለያዩ ንፈኛዉ በሚጠቀምባቸዉ ሚዲያዎች ቪ.ኦ.ኤን ጨምሮ መታወጁ የህ/ዉሳኔዉን ታማኒነት ጥያቄ ምልክት እንዲኖረዉ አድርጎታል፡፡ በመሆኑም እነሱ እንደሚሉት ምርጫ ቦርድ ሚያወጣዉ ዉጤት ብአዴን/ቤተአማራ አሸነፍን በማለት ከሚያራግበዉ ጋር ከተመሳሰለ ምርጫዉ አስቀድሞ የተጭበረበረና ያ ለመብቱና ለነጻነቱ ቅማንት እንጅ ማይመለከተኝ አማራነት ሊለጠፍብኝ አይገባም በማለት 26 አመት ሙሉ ለታገለዉ፤ ብአዴን/ቤትአማራ ጦር አዝምቶ በጠራራ ጸሃይ የታረደ፣ንብረቱ በሳት የወደመበት ለመተማ፣ለቋራና ለጭልጋ ህዝብ እንደ ስድብና ንቀት የሚቆጠር ይሆናል፡፡የምርጫ ሂደት እንደዚህ ባደባባይ ከህዝብ ሚነተቅ ከሆነ ሃገሪቱና ፌዴራላዊ ስርአቱ አደገኛ ሁኔታ ዉስጥ ያለ ስለመሆኑ ግልጽ ማሳያ ነዉ፡፡
ዉድ የቅማንት ምሁራን ተማሪዎችና ወጣቶች፡-
የቅማንት ህዝብ ከሰሜን ጎንድር የአማራ ህዝብ ጋር አንድ ደም ያለዉ ህዝብ ነዉ፡፡በመሆኑም ለቅማንት አጎራባች የሆነዉ የአማራ ወንድም ህዝብ በአካባቢና በተለያዮ ታላላቅ ህዝባዊ ዉይይቶች ላይ ለመንግስት አቋሙን ግልጽ አድረጓል “ቅማንት የጠየቀዉ ህገ-መንገስታዊ ጥያቄ መብቱ ነዉ መልሱለት የምታጋድሉንና ለማቃቃር የምጥጥሩት እናንተ ናችሁ”በማለት ለብአዴንና ለጽንፈኞች ግልጽ በማድረግ ለቅማንት ህዝብ ያለዉን አጋርነት ግልጽ አድረጓል፡፡ብአዴንም ይህ ታላቅ ያማራ ህዝብ የሱን የከፋፋይነትና ትምክታዊ ጽንፈኝነት ስላልተቀበለ እራሱ በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለዉን ሴራ በታላቁ ያማራ ወንድም ህዝብ ላይ ለማላከክ ይሞክራል፡፡ይሁን እንጅጅ ብአዴን በሁለቱ ወንድም ህዝቦች ላይ ደገሰዉን የማፋጀት ሴራ ሁለቱ ህዝቦች በመነጋገር አክሽፈዉታል፡፡
ከላይ ለመግለጸ እንደሞከርኩት ብአዴን የቅማንትን ህዝብ እንደ ቤህራዊ ጠላት በመቁጥርና ከተለያዩ አገር የከዱ የግብፅና የኤርትራ ቅምጦች ጋር በመቀናጀት በህዝባችን ላይ ከዘር ማጽዳት ወንጀል እስከ ማፈናቀል ማዋከብና ሁሉን አቀፍ የሆነ የሰባዊ መብት ጥሰትና ረገጣ በህዝባችን ላይ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ከዚህ ቀደም ቅማንት መባላችንን ፈርተንና ተሸማቀን ስለአንድነታችን በጋራ መወያየት አልቻልነም ነበር፡፡አሁን ግን እደሜ ለባዴንና ለጽንፈኞች የቅማንትን ወጣቶችና ምሁራን ከዚህ ጨምድዶ ከያዘን ቆፈን ተላቀን መሰደቢያችን የነበረዉ ስማችንን በኩራት እኔ ቅማንት ነኝ በማለት ለመብታችን በያለንበት በመታገል ላይ እንገኛለን፡፡ምናልባትም አሁንም “ቅማንት የእንጨት ፍሬ” ላለመባል እራሳችሁን የደበቃችሁና በህዝባችን ላይ የሚፈጸመዉን መብት ረገጣ አሻግራችሁ የምታዩ ካላችሁ ታሪክ ይፋረዳችኋል፡፡እናንተ እንኳን ዝም ብትል ብአዴንና ትምክተኞች ከማሳደድ አይቦዝኑም፡፡አሁን በሰሞኑ በቅማንት ታላላቅ ምሁራን ላይ ስማቸዉን በመዘርዘርና ፎቷቸዉን በየማህበራዊ ሚዲያዉ በመለጠፍ በአለማቀፍ ጽንፈኛ ሚዲያዎች ጭምር ስማችዉ እየተብጠለጠለ እንደሆነ እየታዘብን ነዉ፡፡ይህ ጉዳይ አስተሳሰባችን ከፍ እንዲልና ትግላችን ወደላቀ ደረጃ ያደርሰዉ እንደሆነ እንጅ ለሴኮን ሊያስቆምን አይችልም፡፡በርግጥ የቅማንትን ምሁራን እነሱ የጠቀሷቸዉ ብቻ ሳይሆኑ ባለማቀፍ ተቋማት፣በሃገር ዉስጥና ከሃገር ዉጭ የሚገኙ ለቁጥር የሚታክቱ ናቸዉ፡፡በምህንድስናዉ፣በህክምናዉ፣በዉትድርናዉ፣በማህበራዊ ዘርፉ…ወዘተ ማለትም እዉቅ       ዶክተሮችን፣ኢንጅነሮችን፣ፓይለቶችን፣ፕሮፌሰሮችን፣የተለያዩ ዬኒቨርሲቲ መምህራኖችን፣ልዩ ልዩ አስተማሪዎችን፣ወታደሮችን፣በመማር ላይ የሉ ለቁጥር የሚታክቱ ወጣቶችንና ልዩ ልዩ ሙያተኞችን…ወዘተ ያፈራና በስነምግባር ኮትኩቶ ያሳደገ ቅማንት ታላቅ ህዝብ ነዉ፡፡
ይህ ሁሉ ምሁራን ቅማንት አፍርቶ እያለ ግን በትምክተኛዉና በተስፋፊዉ ቡድን ከሚደርስበት ዱላ ግን ሊያስጥለዉ አልቻለም፡፡በመሁኑም ለምን የሚል ጥያቄ በማንሳት እራሳችንን ልንጠይቅ ይገባናል፡፡ በእኔ እምነት በቅማንት ህዝብ ላይ ይህ ሁሉ በትር የሚያርፍበትና ጥይት ባለማቋረጥ የሚተኮስበት የቅማንት ህዝብ ስላልተደራጀና እኛ ልጆቹ የህዝባችንን በደልና ሰቆቃ በየጥሻዉ ተደብቀን ተመልካች በመሆናችን ነዉ፡፡ በግልጽ እንደሚታየዉ ክልሉን ከሚመራዉ ብአዴን/ቤተኣማራ ጀምሮ ለዴሞክራሲና ለነጻነት ቆመናል የሚሉ ሃይሎች በሙሉ እንደ አንድ በመሆን በቅማንት ህዝብ ላይ ከግድያ ጀምሮ የጥላቻ የእባብ መርዛቸዉን ባንድ 2 ሚሊዮን በሚሆን ህዝብ ላይ ዘር ተኮር የሆነ ተግባር ይፈጽማሉ፡፡ከኢትዩጵያ ሰባዊ መብት ኮሚሽን ዉጭ አንድም ቡድን ወይም የፖለቲካ ድርጅት በቅማንት ህዝብ ላይ የተፈጸመዉንና እተፈጸመ ያለዉን የዘር ማጽዳት ዘመቻ ያወገዘ የለም፡፡
ጽንፈኛ ቡድኖች እየነገሩን እንዳለዉ ምንም እንኳ የቅማንት የራስ አስተዳደር ቢመሰረት እንኳን በብአዴን እስከተገዛን ድረስ ከሚሰነዝሩት ዱላ ወደፊት እንደማናመለጥ አስረግጠዉ እየነገሩን ይገኛሉ፡፡ደሞም ትክክል ናቸዉ በዋግ ህምራና በአዊ አስተዳደር እየተፈጸመ ያለዉን እኩይ ተግባር ማየቱና ማጤኑ ብቻ በቂ ነዉ፡፡በቅማንት ህዝብ ላይም የታሰበዉ የከዉ ነዉ፡፡ ብአዴን የቅማንትን ህዝብ እንደ ቤህራዊ ጠላት አድርጎ ፈርጆ መላክ አስቀምጦ ይመራናል ወይም የልማትና ዴሞክራሲ ጥማታችንን እንድንወጣ ያደርግልናል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነዉ፡፡ይልቁንም እንደነ በየነ አስማረና አቡኔ ብሩ አይነቶችን በቅማንትነታቸዉ የሚያፍሩና አደርባዩችን ሙሰኞችንና ደካሞችንችን በቅማንት ህዝብ ትክሻ ላይ በመጫን ከላይ እንደጠቀስኳቸዉ የቤህረሰብ አስተዳደሮች በጅ አዙር መግዛቱንና ጭቆናዉን በስመ የራስ አስተዳደር በረቀቀ መንገድ እንዲያስቀጥል ሰፊ እድል ይሰጠዋል፡፡
በመሆኑም እኛ የቅማንት ልጆች አንድ ሆነን እስካልተደራጀን ድረስ ራስ አስተዳደሩ መፍትሄ እንደማይሆን ከህዝበ ዉሳኔዉ በኋላ በቅማንት ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለዉ ዛቻና ግድያ ትልቅ ማሳያ ነዉ፡፡ በመሆኑም ለዉይይት የሚከተለዉን ዘላቂ የመፍትሄ ሃሳቤን አቀርባለሁ፡-
መፍተሄዉም ከብአዴን/ቤተአማራ ጋራ ህጋዊ ፍች መፈጸም ነዉ፡፡የቅማንት ልዩ አስተዳደር በሃቀኛና ህዝቡ እራሱ በቀጥታ በሚመርጣቸዉ ሃቀኛ ልጆቹ መተዳደር ይገባዋል፡፡ያን ለማድረግ ደግሞ የቅማንት ህዝብ የሃገሪቱን ህገ-መንግስት የተቀበለና ያከበረ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ አደረጃጀት ያስፈልገዋል፡፡ይህንንም ልምድ ከአርጎባ ህዝብ መዉሰድ ያስፈልጋል፡፡የአርጎባ ህዝብ የራሱ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ድርጅት ባለቤትና የኢህአዴግም አጋር ድርጅት ነዉ፡፡በመሁኑም ያለማንም ጣልቃ ገብነት ከቀበሌ ጀምሮ፣የተወካዮች ም/ቤትና ፌዴሬሽን ም/ቤት እራሱ ህዝቡ በቀጥታ የመረጣቸዉ የራሱ ልጆች በፍታዊነት ተወክለዋል፡፡ይህ በመሆኑም ቤህረሰቡ ያለማንም ጣልቃ ገብነት እራሱን በማስተዳደር፣ለመጥፋት ተቃርቦ የነበረዉን ቋንቋዉንና ባህሉን በማሳደግ በተዘረጋዉ ፈዴራላዊ ስርአት ተጠቃሚ እየሆነ ይገኛል፡፡
ቅማንት ባለመደራጀቱ የተነሳ ስለቅማንት መብት ጥያቄ የሚያነሳ የቅማንት ልጅ ሁሉ የህወሃት ተላላኪ እየተባለ በመሰደብና ባሉበት ግደሏቸዉ አዋጅ በጅምላ እየታወጀብን ይገኛል፡፡ባጠቃላይ ብአዴን ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በመቀናጀት በቅማንት ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለዉ ዘርን መሰረት ያደረገ ግድያ እነ መላኩ ተፈራና ገዛከኝ ወርቄ በህዝባችን ላይ ካደረሱት ጭፍጨፋ በእጅጉ የከፋ ነዉ፡፡እነዚህ ሁሉ አስገዳጅ ምክኒያቶች የቅማንት ህዝበ የራሱ መሪ ድርጅት ከላይ እንደጠቀስኩት እንደ አርጎባ፣ቤኒሻንጉል፣ሃረሪ፣ጋንቤላ፣ሶማሌ፣አፋር፣…ወዘተ ህዝቦች እራሱን በራሱ የመምራትና ሙሉ የፖለቲካ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
የቅማንት ምሁራንና ወጣቶች ይህን ማድረግ ካልቻልን ህዝባችን በስመ የራስ አስተዳደር አሁን እየተደረገብን ካለዉ የከፋና የቅማንት ምሁራን እና ታጋዮችን የቻለዉን ሰሞኑን ገለድባ ከተማ ላይ እንደፈጸመዉ ወንድማማቾች ግድያ እንዲገድልና የቀረዉንም በህግ ሽፋንና የመንግስትን መዋቅር በመጠቀም ወደዘብጥያ እንዲያወርዳቸዉ እድል እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ልጆቻችን ቅማንት ሆነዉ እያለ የማይመለከታቸዉን “…የአማራነት ክብር..”የሚል በማንነት ላይ ተመሰረተ የማይወክለንን መዝሙር በየት/ቤቱ እየዘመሩ ስለማይመለከታቸዉ ማንነት በስመ መዝሙር የስነ-ልቦና ተጠቂዎች እንዲሆኑ መፍቀድ ይሆናል፡፡ከላይ ያለዉን አደረጃጀት እስካልፈጠርን ድረስ በፌደራል ስርአቱ መጠቀምና ለናፈቀንና እንደ ሰማይ ለራቀን ዴሞክራሲ ባህልንና ያካባቢያችንን ልማት ማምጣት ህልማችን እንደሆነ አለም ጥላን ትኮበልላለች፡፡
በመጨረሻም የቅማንት ምሁራንና ደጋፊዎቻችን ባቀረብኩት ሃሳብ ላይ በያላችሁበት በመነጋገር ድጋፍ ወይም በአመክንዩ ላይ የተመሰረተ ክርክር እንድታደርጉበት አበክሬ እያሳሰብኩ ለዴሞክራሲና ለፍትህ መስፋፋት እየታገላችሁ ያላችሁ ቤህር ቤህረሰቦች ምንም እንኳ እናንተ እኛ እየተጋፈጥን ያለዉን ዘረኝነትና ትመክታዊ ስርአት ከ 26 አመት በፊት አሽቀንጥራችሁ የገረሳችሁት ቢሆንም የቅማንት ህዝብ ግን የናንተን አድል ማግኘት እንደ ሰማይ እርቆት ይከዉ ከ26 አመት በኋላም በሰቆቃ ዉስጥ ይገኛል፡፡በመሆኑም የቅማንት ህዝብ ሙሉ በሙሉ የዴሞክራሲያዊ ስርአቱ ተጠቃሚ እንዲሆንና በሃገራችን ላይ እያንዣበበ ያለዉ ጽንፈኝነትና ትምክታዊ አስተሳሰብ ከቅማንት ደል ጋር ግብአተ መሬቱ እንዲፋጠን ከቅማንት ህዝብ ጎን የመሰለፍ የታሪክና የዜግነት ግደታ አለባችሁ፡፡

ልጅ አለማየሁ ቴዎድሮስ

ድል ለታጋሹና ለጨዋዉ የቅማንት ህዝብ ሞት ለጽንፈኖችና ለትምክህት!!

Leave a Reply